Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል የወንዶገነት ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የወንዶገነት ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት የሚሆን የስንቅ ዝግጅት እና የደም ልገሳ መርሃ ግብር አከናውነዋል፡፡

ድጋፉ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ 26 ሺህ ብር የሚገመት የስንቅ አይነት ሲሆን፥ 65 ዩኒት የሚሆን ደም ለግሰዋል፡፡

እስከ ግንባር ድረስ በመዝመት የህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ ሲሉ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ለመከላከያ ሠራዊት ለስንቅ የሚሆን ገብስ ከማሰባሰብ ጀምሮ እስከ ዝግጅቱ መሳተፋቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ፥ መከላከያ ለአገሪቷ ብሎ እየተዋደቀ እኛ ዝምታን መምረጥ የለብንም ብለዋል።

ከዚህ ቀደምም ሰዎችን በማስተባበር ለመከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ የሚገኙት ነዋሪዎች አገራችን ሠላም እስከምታገኝ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ቃል ገብተዋል ነው የተባለው፡፡

በታመነ አረጋ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.