Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሚገኙ የትምህርት ማህበረሰብ አባላት ለተፈናቃዮች 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስአበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ የትምህርት ማህበረሰብ ክፍሎች ተፈናቅለው በደብረብርሃን ከተማ ለሚገኙ ወገኖች 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አበረከቱ።

ድጋፉን ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እንዳሉት፥ በአዲስ አበባ የሚገኙ ከትምህርት ማህበረሰብ የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ የምግብ ግብዓቶች ፣ የተማሪዎች ቁሳቁስ፣ የንጽህና መጠበቂያዎችን አካቷል።
የተከፈተብን ጦርነት እንደ አገር በመሆኑ በጋራ ጠላታችንን እንመክታለን ተብለዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል በበኩላቸው፥ ለተደረገውን ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በዞኑ300 ሺህ ተፈናቃይ በመኖሩ ድጋፎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርባቸው አመላክተዋል።

በሰላማዊት ሙሉነህ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.