የሀረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ
አዲስ አበባ፣ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች የአሸባሪውን የህወሃት ኃይል ለመደምሰስ በህልውና ዘመቻ ላይ መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ደም ለግሰዋል፡፡
ለሀገር መቆም ማለት ግንባር ድረስ በመሄድ ከጠላት ጋር መፋለም ብቻ ሣይሆን ለሀገሪቱ እድገት ሁሉም በያለበት ተቋም እና ስራ ህብረተሰቡን በንቃትና በታማኝነት በማገልገል ማስመስከር እንደሚገባም ነው ሠራተኞች የገለጹት፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለዘመናት በክብር የቆየችውን ኢትዮጵያን ሉአላዊነቷ እንደተከበረ እንዲቆይና ለቀጣዩ ትውልድ ነፃነቷ የተከበረን ሃገር ለማውረስ ከጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ጎን ለመቆም ጦርነቱን በግንባር በመገኘት መምራት በመጀመራቸው ለኛ የወኔ ስንቅ ነውና በተቋማችን መከላከያ ከመደገፍ ባሻገር ስራችንን ከምንግዜውም በላይ በትጋትና በታማኝነት ለመፈጸም ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡
የሀረሪ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች ከደም ልገሳው ባሻገር በጦርነቱ ምክንያት ከአማራና አፋር ክልሎች ከቤት ንበረታቸው ተፈናቅለው በተለያዩ ጊዜያዊ መጠለያዎች ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች የተለያዩ የአልባሳትና የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በቲያ ኑሬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!