በካሊፎርንያ ግዛት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ካሊፎርንያ ግዛት ቤይ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከ10ሚሊየን ብር በላይ በተለያዩ አካባቢዎች በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ የማህበረሰብ ክፍል ድጋፍ አደረጉ፡፡
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እየተዋጋች ትገኛለች፤ ይህ የእጅ አዙር ጦርነት በአንድም በሌላም መልኩ ማህበረሰቡን እየጎዳ እና እያፈናቀለ በመሆኑ ተፈናቃዮች መደገፍ እንደሚገባ በመጠቆም÷ ለዚህም በውጭ የሚኖሩ ዳያስፖራ ዎች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና ይገባል ሲሉ የአደጋ ስጋት አመራር ምክትል ኮሚሽነር ነሲቡ ያሲን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለገጠማት ጊዜያዊ ችግር በውጭ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ከመንግስት ጎን በመሆንአስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ፍቃደኛ መሆናቸውን በአሜሪካ ካሊፎርንያ ግዛት ቤይ አካባቢ አስተባባሪ አቶ ምኒልክ አንዳርጌ ገልጸዋል፡፡
ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ነሲቡ ያሲን ጠይቀዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!