Fana: At a Speed of Life!

“በቃ!” የሚለው የኢትዮጵያ ድምፅ ሰፊ ተቀባይነት እያገኘ ነው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ያሳለፍነው ሳምንት የተለያዩ የአፍሪካና የሌሎች ክፍለ ዓለማት አገሮች ከኢትዮጵያ ጎን መቆማቸውንና “በቃ” በሚል መርህ የተካሄደው የኢትዮጵያ ድምፅ ሰፊ ተቀባይነት እያገኘ መሆኑን ያረጋገጥንበት ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ፥ ኢትዮጵያ ዳግም የአፍሪካ የነፃነት ትግል አርማ ሆና መውጣቷን ገልጸዋል።
“በቃ!” በሚል በተከላሄደው ዓለም አቀፍ ንቅናቄ ኢትዮጵያውያን፥ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ባሰሙት የጋራ ድምጽ÷ ለአዲሱ ቅኝ አገዛዝ አንንበረከክም ብለዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ንቅናቄውም ኢትዮጵያ በርካታ ወዳጆችን ያተረፈችበት መሆኑንም ነው የገለጹት።
ነፃነታችንን በስንዴ እንደማንለውጥም ለማስገንዘብ ተችሏል ነው ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.