አሸባሪዎቹን ቀብረን ጠንካራ ዲሞክራሲን እንገነባለን – አቶ ከድር ጃዋር
አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የህወሓት አሸባሪዎችን እና ቡችላዎቻቸውን ከሥሩ አስወግደን በኢትዮጵያ ጠንካራ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን እናስቀጥላለን ሲሉ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጃዋር ተናገሩ፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጃዋር አዲስ ለተመሰረተዉ የድቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸዉም ÷ ትክክለኛ የፌደራል ስርዓት ሰዎች የራሳቸውን መንግስት የሚገነቡበት ስርዓት ነው ብለዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ 11ኛ ክልላዊ መንግስት ሆነዉ መመስረታቸዉ በሃገሪቱ ያለዉ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እያደገ መሆኑን ማሳያ ነዉ ብለዋል፡፡
ስለሆነም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች በድሬዳዋ ከተማ አሰተዳደሩ ስም የእንኳን ደስ አላቹ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ከንቲባዉ፡፡
የኢትዮጵያን አንድነት የሚከፋፍሉ የህወሓት አሸባሪዎችን እና ቡችላዎቻቸውን ከሥሩ አስወግደን በሀገሪቱ ጠንካራ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን እናስቀጥላለን ሲሉ መናጋራቸውን ከከተማ አሰተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!