የአራዳ ክፍለ ከተማ የዘማቾች ሽኝት በጃን ሜዳ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እና የዘማቾች ሽኝት መርሃግብር በአራዳ ክፍለ ከተማ አዘጋጅነት በጃን ሜዳ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሀግብሩ ላይ ሽኝት የሚደረግላቸው ዘማቾችም ”ከመሪያችን ጋር እንዘምታለን ፤ ሀገራችንን እንጠብቃለን ፤ ሰላሟን እና ደህንነቷን እናረጋግጣለን” በማለት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
እናቶችም ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ እና በግንባር ለሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ሁሎ ስንቅ እያዘጋጁ ሲሆን ÷ ”ከመሪያችን ጎን ሁነን እስከመጨረሻው ድርስ ስንቅ በማዘጋጀት ለሀገራችን እንቆማለን” ብለዋል።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎችን በማስተባበር ለ3ኛ ዙር ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ድጋፍ የሚሆን ከ83 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል።
በአዲስ ሙሉነህ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!