Fana: At a Speed of Life!

የደብረብርሃን ከተማ ማህበረሰብ አካባቢውን በንቃት እየጠበቀ ይገኛል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረብርሃን ማህበረሰብ አካባቢውን በንቃት እየጠበቀ ይገኛል ሲሉ የከተማዋ ሰላምና ደህንነት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ ተናገሩ።
ወቅቱ የህልውና አደጋ እንደህዝብ የተጋረጠብን ነው ያሉት አቶ ዳንኤል እሸቴ፥ የከተማው ማህበረሰብ ይህን በመረዳት ሰላሙን በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ጁንታው በተሳሳተ መረጃ በርካታ ዜጎችን ሲያፈናቅል መቆየቱን በማስታወስ፥ የከተማው ወጣት ከፖሊስ እና የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በጥምረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አያይዘውም በሌሎች የክልሉ ከተሞች እንደተደረገው ሁሉ ጁንታውን ለመመከት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሁን ያለው ሰላምን ለማስጠበቅ መንግስት ከወጣቱ እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።
በኤልያስ ሹምዬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.