Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት በመቻቻል ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት በመቻቻል ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው።
ውይይቱ እየተካሄደ ያለው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የመቻቻል ቀን ምክንያት በማድረግ ነው።
“የመቻቻል ባህል አንድነትን ለማጠናከር ያለው ፋይዳ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ያለው `16ኛው የጉሚ በለል ውይይት፥ በኢትዮጵያ የመቻቻልና አብሮነት እሴቶችን በማጎልበት ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ ያተኮረ ነው።
የኦሮሞ ሕዝብ በባህሉና በቆየው የገዳ ስርአቱ መቻቻልንና አቃፊነትን በማስቀጠል ከሌሎች ብሔር ብሄረሰቦች ጋር እንዴት አብሮ ሲኖር እንደነበርና ለወደፊቱም በልዩነት መሐል ጠንካራ አንድነትን ለአገራዊ ግንባታ ማዋል በሚቻልበት ዙሪያ ሃሳቦች እየተነሱ ነው።
በዚሁ 16ኛው የጉሚ በለል ውይይት የባህል ባለሙያዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና አባ ገዳዎች ተሳትፈዋል።
የጉሚ በለል ውይይት በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚዘጋጅና ባለሙያዎችና የሚመለከታቸው አካላት የሚያካሂዱት ውይይት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.