Fana: At a Speed of Life!

ሀሰተኛ መረጃ በሚያሰራጩ የሚዲያ ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል – አቶ መሐመድ ኢድሪስ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ያስቀመጣቸውን ህገ-ደንቦችና የሙያውን ሥነ ምግባር በመጣስ ሀሰተኛ መረጃ በሚያሰራጩ የሚዲያ ተቋማት ላይ የሚወሰደው የእርምት እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አስታወቁ።

በኢትዮጵያ በተለያዩ ዓለማቀፋዊ ቋንቋዎች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተደራሽ የሚሆን ሚዲያ ባለመኖሩ፥ ዓለም የኢትዮጵያን እውነት እንዳይገነዘብ ማድረጉም ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መሐመድ ኢድሪስ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ÷ አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን የህልውና ዘመቻውን አስመልክቶ ስለ ኢትዮጵያ የተዛቡ ዘገባዎችን ሲያሰራጩ መቆየታቸውን አውሰተዋል፡፡

እነዚህ መገናኛ ብዙሃን የሚያሰራጩት ዘገባ እና እውነታው በጭራሽ የተለያዩ መሆናቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ÷ የፖለቲካ ፍላጎታቸዉን ለማሟላት በተቀናጅ መልኩ የሀሰት ዘገባዎችን ሲያሰራጩ መቆየታቸዉን ተናግረዋል፡፡

በዚህም እሳቸው የሚመሩት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ያስቀመጣቸዉን ህገ-ደንቦች በጣሱ የምዕራባዉያን መገናኛ ብዙሃን ላይ የማሰጠንቀቂያ ደብዳቤ መፃፉን አውስተዉ ÷ በቀጣይም በሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት በተሰማሩ የሚዲያ ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በአገራችን በተለያዩ ዓለማቀፋዊ ቋንቋዎች ለሁሉም ተደራሽ የሚሆን የሚዲያ ተቋም ባለመኖሩ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን እውነት እንዳይገነዘብ ማድረጉንም ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡

በሀገር ውስጥ በአረበኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በፈረንሳይኛ ቋንቋዎች ዘገባዎችን የሚሰሩ ሚዲያዎች ቢኖሩም፥ በሀገሪቱ ዋና ዋና መገናኛ ብዙሃን ተፅዕኖ ስር በመሆናቸው በትኩረት እንዳልተሰራባቸዉ ተናግረዋል ፡፡

ስለሆነም ችግሩ እሰከሚቀረፍ ድረስ በዓለማቀፍ ደረጃ ተሰሚነት ያላቸዉ ግለሰቦችና ድርጅቶች የጀመሩትን የኢትዮጵያን እውነትና ትክክለኛ ገጽታ ለዓለም አቀፉ ማህበረስብ የማሳወቅ ዲፕሎማሲያዊ ስራ አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸዉ ጉዳይ ላይ የተሳሳተ መረጃ በሚሰሙበት ጊዜ ሊቃወሙና እዉነታዉን የማሳወቅ ስራ በትብብር መስራት እንደሚገባ ማሳሳቢያ ሰጥተዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.