Fana: At a Speed of Life!

ሴት ጋዜጠኞች ያዘጋጁትን 100 ኩንታል ስንቅ ለመከላከያ ሠራዊት አበረከቱ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስት ሴት ጋዜጠኞች ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ባሰባሰቡት ከ700 ሺህ ብር በላይ ያዘጋጁትን 100 ኩንታል የበሶ ስንቅ ለአገር መከላከያ ሰራዊት አበረከቱ።
 
ድጋፉን የመከላከያ ሚኒስቴር የሴቶች ዘርፍ ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ ተረክበዋል፡፡
 
የከተማ ልማትና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በድጋፍ ማስረከቡ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተዋል፡፡
 
ዶክተር ኤርጎጌ በዚሁ ጊዜ የአገር ግንባታ ተግባር ላይ በማዋል አገርን የማዳን ታሪካዊ ሃላፊነት ተጥሎብናል ብለዋል፡፡
 
ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒም ኢትዮጵያ ሁልጊዜም ታልፋለች፤ የገጠሙንን ችግሮች በጋራ እናልፋልን፤ የአሸባሪውን ቡድን እኩይ ዓላማም እናከሽፋለን ነው ያሉት።
 
የአገርን ህልውና ለማረጋገጥ መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም ተናግረዋል።
 
ሜጀር ጄኔራል ጥሩዬ የመከላከያ ሠራዊቱ ጠንካራ ደጀን ስላለው በጥሩ ሞራል እየገሰገሰ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
 
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.