Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ አየር ክልል የሚደረግ በረራ ሁሉ ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ ነው – ሲቪል አቪየሽን

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ወደ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያም ሆነ በየትኛውም የኢትጵያ አየር ክልል ላይ የሚደረግ በረራ ሁሉ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከስጋት ነጻ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ  በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ አየር ክልል የሚደረግ በረራ ስጋት እንዳለበት ተደርጎ የተሰራጨው መረጃ መሰረተ ቢስና ከዕውነታው የሚቃረን መሆኑንም አመላክቷል፡፡

የአገሪቷ የአየር ክልል እና አየር መንገዱ ፍጹም ደህንነቱ የተጠበቀ ለመሆኑ ለተጠቃሚዎቻችን እናረጋግጣለንም ብሏል።

ዓለም አቀፍ የጥንቃቄ እና ደህንነት ደረጃ መስፈርት በሚያዘው መሰረትም የተጠቃሚዎቻችን ምቾትና ደህንነት ተጠብቆ ከሥጋት ነጻ የሆነ በረራ እንዲያደርጉ የጥንቃቄ መስፈርቶችን እንደወትሮው ሁሉ እንደሚተገብርም ባለስልጣኑ አስታወቋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.