የሀረሪ ክልል እናቶች በህልውና ዘመቻው ከመከላከያ ሠራዊት ጎን መሆናቸውን ገለፁ
አዲስ አበባ፣ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል እናቶች አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ እየተደረገ በሚገኘው የህልውና ዘመቻ ከመከላከያ ሠራዊት ጎን መሠለፋቸውን ገለፁ፡፡
የክልሉ የብልፅግና ፖርቲ ሴቶች ሊግ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተወያዩ ሲሆን÷ ቡድኑ ህዝብን ለማሸበር የሚያደርገው ጥረት እንዳይሳካ አካባቢያቸውን በትጋት እንደሚጠብቁም ነው እናቶች የተናገሩት።
ለጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት ከአሁን በፊት በስንቅ ዝግጅትና በተለያየ መንገድ ድጋፍ ማድረጋቸውን የገለፁት እናቶቹ÷ አሁንም ልጆቻቸውን ወደ ጦር ግንባር ለመላክ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ፅንፈኛው በወረራቸው አከባቢዎች ሴቶችን በመድፈር ፀረ ኢትዮጲያዊነቱን አረጋግጧል ያሉት ደግሞ÷ የሀረሪ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ አደረጃጀት አረፉት ኢብራሂም ናቸው።
ህወሓት ወደ መቃብር እያደረገ ባለው ጉዞ በርካታ ቅርሶችን ማቃጠሉ አሸባሪነቱን በይፋ ያረጋገጠ መሆኑን የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፖርቲ ሃላፊ አቶ አብዱልጀባር መሀመድ ገልፀዋል።
ይህንን ቡድን ወደ ተመኘው ሲኦል ለመሸኘት እየተደረገ ባለው ጥረት የክልሉ ሴቶች ከጀግናው መከላከያ ሠራዊት ጎን እንዲሰለፉ ሃላፊው ጠይቀዋል።
በምንያህል መለሰ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!