በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከ100 በላይ ሰርጎ ገቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወራሪውን ህወሀት የሽብር እንቅስቃሴ ለመከላከል በተሰራ አካባቢን ነቅቶ የመጠበቅ ተግባር እስካሁን ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰርጎ ገቦች መያዛቸውን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ሀይለማርያም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ እየተሰራ ባለው አካባቢን ከሰርጎ ገቦች የመጠበቅ ተግባር 100 ያህል ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል።
እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለፃ፥ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ሸፍተው ጨካ የገቡ ግለሰቦች ጭምር የህግ ጉዳያችን ከዘመቻ መልስ ሊታይ ይችላል ፥ አሁን ግን ሀገራችንን ለማፈራረስ አልሞ የተነሳውን የአሸባሪ ቡድን ለማጥፋት ግንባር መገኘት አለብን በማለት የዘመቻው አካል መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዞኑ የሚገኙ የሚሊሻ አባላትም በክልሉ ሶስት ግንባሮች ተሰልፈው ጠላትን እየደመሰሱ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች የህልውና ዘመቻውን በመቀላቀል ከሚያደርጉት ሀገራዊ ተሳትፎ በተጨማሪ በስንቅ ዝግጅትና ድጋፍ ደጀንነታቸውን እያሳዩ ነውም ብለዋል።
ወደፊትም ግንባር በመዝመት፣ የስንቅ ዝግጅት በማድረግና አካባቢን በመጠበቅ መላው የዞኑ ህዝብ ሃላፊነቱን እንደሚወጣ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ሙሉጌታ ደሴ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
–
Distribution score
Boost post
Like
Comment
Share