የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ለምልምል ሰልጣኞች ወታደራዊ እውቀታቸውን እያካፈሉ ነው
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዝዋይ ቡልቡላ ማሰልጠኛ ማዕከል ከአራቱም አቅጣጫ የመጡ ምልምሎችን በማሰልጠን ሂደት ጥሪ የተደረገላቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት አኩሪ ተግባር እያከናወኑ እንደሚገኙ ተመላከተ።
የማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ሰቦቃ በቀለ፥ አሰልጣኞቹ ተቋሙ ለሚፈልገው አላማና ግብ ስኬታማ ውጤቶችን ለማስመዝገብ በትጋት ፣ በቁርጠኝነትና በታታሪነት በመስራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል ብለዋል።
አሸባሪው በአገራችን ላይ በፈፀመው ጥቃት አገሬን አላስነካም በማለት ከሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫዎች ለተሰባሰበው ወጣት ትክክለኛውን ወታደራዊ ሳይንስ በማሰልጠን ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
በማዕከሉ የ21ኛ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ሻለቃ ደምሴ ነጋሽ ፣ ሻምበል አዛዥ መአቶ አለቃ ፀጋው ድረስ እና መቶ አለቃ ሃይለማሪያም በቂ እንዳሉት፥ ለ27 አመታት እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረን ነበር።
አሁን በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ወደ መከላከያ ሰራዊቱ ተቀላቅለው በህልውና ዘመቻ በመሳተፍ የነበራቸውን የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ዕውቀት አሁን ለሚሰለጥነው ሰራዊት በማካፈላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አሰልጣኞቹ አሁንም መተኪያ የሌላትን ህይወታችንን ለመስጠት ዝግጁ ነን ብለዋል በሰጡት አስተያየት።
ዛሬም እንደጥንት አባቶቻችን አንድ በመሆን ከደጀን ህዝባችን ጋር አብረን በመሆን ይህን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!