ሁለቱ ክፍለ ከተሞች ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የአይነት ድጋፍ ለተፈናቃዮች አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቂርቆስና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ቁሳቁስ ድጋፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ።
ክፍለ ከተሞቹ በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) አስተባባሪነት በአማራ ክልል በአሸባሪውና ወራሪ የህውሃት ኃይል ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ አልማ ድጋፍ ሲያሰባስብ መቆየቱን የአዲስ አበባ የአልማ ቂርቂቆስ ክፍለ ከተማ አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ምሕረቱ እና የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተባባሪ አቶ አንዳርጌ ተዋበ ተናግረዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ 6 ነጥብ 3 ሚሊየን እንዲሁም ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደግሞ ከ2 ነጥብ 3 በላይ ግምት ያለዉ ምግብ፣ እህልና ሌሎችንም ቁሳቁሶች በባሕር ዳር ዘንዘልማ ጊዜያዊ ጣቢያ በመገኘት ለተፈናቀሉ ወገኖች አበርክተዋል፡፡
በዘንዘልማ ጊዜያዊ የተፈናቀሉ ወገኖች ማስተባበሪያ የሰሜን ወሎ ዞን ተወካይ አቶ ሞገስ ቸርነት የተደረገዉን ድጋፍ ሲቀበሉ ድጋፉ ኢትዮጵያዊያን አንድ መሆናችንን የሚያሳይ ተግባር ነዉ ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ሁሉም የሀገሪቱ ዜጋ በመጠለያ ጣቢያዎች በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ዉስጥ የሚገኙ ወገኖችን እንዲደግፍ በመጠየቅም ወጣቶች ወደ ጦር ግንባር በመዝመት ጠላትን እንዲፋለሙ ጠይቀዋል አቶ ሞገስ ፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን