አዲስ አበበ፣ ህዳር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ዞን በህልውና ዘመቻው በግንባር እየታገለ ላለው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለአምስተኛ ጊዜ የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡
ዛሬ ለአምስኛ ዙር በተደረገዉ ድጋፍ÷ ከ 14 ሚሊየን ብር በላይ ብር በመከላከያ አካውንት ገቢ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም 370 ሰንጋዎች፣ 332 ፍየሎችና በጎች እንዲሁም 10 ነጥብ 5 ኩንታል ስኳር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ 199 ዩኒት ደም ልገሳም ተደርጓል፡፡
የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ የዞኑ ነዋሪዎች ለመከላካያ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ በቀጣይም ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡
በማቱሣላ ማቴዎስ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!