Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት የሚፈጽመው ውድመት በምዕራባውያን ውግዘት አልገጠመውም – በተመድ የኤርትራ አምባሳደር

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያን በአፍሪካ ቀንድ በሚከተሉት የተሳሳተ የውጪ ፖሊሲ ምክንያት አሸባሪው ህወሓት የሚፈጽማቸውን ውድመቶች እያወገዙ እንዳልሆነ በተባበሩት መንግስታት የኤርትራ አምባሳደር ሶፊያ ሃይለማርያም ተናገሩ፡፡

አምባሳደሯ አር ቲ ከተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት፥ አሸባሪው ህወሓት የሚፈፅማቸው ጅምላ ጭፍጨፋዎችና የመሰረተ ልማት ውድመቶች በምእራባውያኑ ዘንድ በዝምታ ይታለፋሉ፡፡

በአንፃሩ የተባበሩት መንግስታት ጭምር እንዳረጋገጠው አሸባሪው እርዳታ ጭነው የሚገቡ መኪኖችን አስቀርቶ ለራሱ ጥቅም ያውላል፣ በምዕራባውያን  የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ከለላ ይሰጠዋል፣ ሳተላይት  እና የሳተላይት መረጃዎችን እንዲያገኝና ወታደራዊ እገዛ የሚያደርጉ ሰዎች ጭምር ይቀርቡለታል ብለዋል አምባሳደሯ፡፡

አሸባሪው ህወሓት ወደ ኤርትራ ሚሳኤል ማስወንጨፉን ተከትሎ አንዳችም ውግዘት አለማስተናገዱን አስታውሰው፥ በአንፃሩ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል በሚል ብርቱ ጫና ለመፍጠር መሞከሩን ገልጸዋል።

“ኤርትራ ባለፉት 20 አመታት በምእራባውያን የሚደርስባትን ጫና ተቋቁማ ቆይታለች” ያሉት አምባሳደሯ፥ ኢትዮጵያም አሁን እያስተናገደች ያለውን ጫና ተቋቁማ ለመውጣት ጥረት ማድረግ እንዳለባት አመላክተዋል።

ምዕራባውያን በሚከተሉት የተሳሳተ ፖሊሲ ገፈት ቀማሽ የሆኑት ኢትዮጵያና ኤርትራ ብቻ ሳይሆኑ ጊኒ እና ማሊ ሰለባ መሆናቸውን ጠቅሰው፥ የአረብ አብዮትም የዚህ የተሳሳተ ፖሊሲ ተጽዕኖ የፈጠረው እንደነበር አስታውሰዋል።

ወቅቱ ኢትዮጵያውያን ግፊቱንና ተፅዕኖውን ተቋቁመው ጣልቃ ገብነትን የሚመክቱበት እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ሰላማዊ ግንኙነት የመጡት በምዕራባውያን ፍላጎት ሳይሆን በራሳቸው ውሳኔና የኢትዮጵያ ህዝቦች አሸባሪውን ህወሓት በትግላቸው ከስልጣን በመሸኘታቸው እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የምዕራባውያንን  የሚዲያ ዘመቻ መቋቋም እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.