Fana: At a Speed of Life!

በውስጣችን መሽገው ከጀርባ የሚወጉንን ባንዳዎች ያለምህረት እንታገላለን- የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በውስጣችን መሽገው ከጀርባ ሊወጉን የሚፈልጉ ባንዳዎች ያለምህረት እንታገላለን ሲሉ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ነዋሪዎቹ የመከላከያ ሠራዊትን በመደግፍ ፣ አሸባሪው የህወሓት ቡድን እና ተላላኪዎቹን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
በሠልፉ ላይ የተሳተፉ የከተማው ነዋሪዎች፣ ሃገር ለማፍረስ የተነሳው አሸባሪው የህወሓት ቡድን መቀበሪያው አሁን በመሆኑ ለዚህም በብሔር ሳንለያይ በጋራ የምንነሳበት ወቅት ነው ብለዋል።
አካባቢያቸውን ከመጠበቅ ጀምሮ የክተት ዘመቻውን ለመቀላቀል ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ፥ በውስጥ መሽገው ከጀርባ ለመውጋት የሚፈልጉ ባንዳዎችን በተደራጀ ሁኔታ እንደሚታገሉም አረጋግጠዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሕዳሴ ግድብ መገኛ በመሆኑ ወጣቶች በተለየ መልኩ ይህንን ሃገራዊ ፕሮጀክት የመጠበቅ ኃላፊነታችን እንደሚወጡም አስረድተዋል።
በሠልፉ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱልሙኒየም አብዱልዋሂድ ፥ የከተማው ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ፣ በአሶሳ ከተማና አካባቢው አሁን ያለውን ሠላማዊ እንቅስቃሴ ለመበጥበጥ የሚሞክሩ የህወሓት ተላላኪ የውስጥ ባንዳዎችን ዓላማ እንዲያከሽፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በአማራ ክልልና አፋር ክልሎች የተፈጠረው የጸጥታ ችግር የሁላችንም በመሆኑ፣ ሃገርን ለማፍረስ የተነሳውን የሽብር ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር በሚደረገው ጥረት የከተማው ነዋሪዎች ከመከላከያ ሠራዊትና ከክልል ሉዩ ኃይሎች ጎን ይቆማሉ ብለዋል።
የከተማው ነዋሪዎች ለመከለከያ ሠራዊት ሲያደርጉት የነበረውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አቶ አብዱልሙኒየም ገልጸዋል።
የአሶሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃሊድ አቡበይድ በበኩላቸው፥ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ወረራ ከፈጸመባቸው የአፋርና አማራ ክልሎች ባሻገር በተለያዩ አካባቢዎች ተላላኪዎቹን ማሠማራቱን ጠቁመው፣ የወረዳ ነዋሪዎች በተደራጀ መንገድ አካባቢውን ሊከታተሉ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ህብረተሰቡ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአግባቡ በመተግበር የበኩሉን ከመወጣት ባሻገር ከጸጥታ አካላት ጎን በመቆም የህወሓት ተላላኪዎችን አጋልጦ እንዲሰጥም ጥሪ ማቅረባቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+4
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.