Fana: At a Speed of Life!

ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ ቁ.1

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ቁጥር 5/2014 መሠረት፣ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 26 ቀን 2014 ሥራውን ጀምሯል።

ዕዙ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ከተነጋገረ በኋላ የሚከተሉትን የመጀመሪያ ውሳኔዎች አስተላልፏል።

1. በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች፤ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪነት መታወቂያ በሕገ ወጥ መንገድ እየተሰጠ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ አረጋግጧል።

በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም የክልልና የከተማ አስተዳደር የነዋሪነት መታወቂያ ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይሰጥ ተከልክሏል።

2. በተደረገላቸው የክተት ጥሪ መሠረት በአሁኑ ወቅት በግንባር ከተሰለፈና ለመዝመት ከተመዘገበ ሰው ውጭ በክልል ከተሞች፣ በዞንና ወረዳ ከተሞች፣ በከተማ አስተዳደሮች፣ እንዲሁም በከተማ ደረጃ በሚታዩ ሌሎች ከተሞች የሚገኝ ማንኛውም መሣሪያ የያዘ ሰው በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ መሣሪያውን እንዲያስመዘግብ ታዝዟል። በተጠቀሱት መስተዳድሮች የሚገኙ ኃላፊዎች በቀልጣፋ አገልግሎት ይሄንኑ እንዲያስፈጽሙ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

3. የገባንበትን የህልውና ጦርነት መመከት የሚቻለው ኢኮኖሚያችንን በማሳደግና ዜጋው የሚጠበቅበትን ግዴታ ሲወጣ ነው።

በመሆኑም ጊዜው የግብር መክፈያ ወቅት ስለሆነ፣ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ሕይወታቸውን ለመስጠት በወሰኑበት በዚህ ጊዜ፣ ግብር ከፋዩ ማኅበረሰብ ለሚወዳት ሀገሩ ተገቢውን ግብር በተገቢው ጊዜ በመክፈል ግዴታውን እንዲወጣ እያስታወቅን፤ ግብር ከፋዩ ማኅበረሰብ ግብር እንዳይከፍል በሚቀሰቅሱትና በሚያሸብሩት ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድባቸው ታዟል።

ከዚህም በተጨማሪ ግብር ከፋዩ ከሕገ ወጥና ከብልሹ አሠራር በጸዳ መልክ ግብሩን እንዳይከፍል በሚያደርጉና አጋጣሚውን ለግል ጥቅም ለማዋል በሚሯሯጡ የግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች ላይ አስፈላጊው ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ ታዟል።

ጥቅምት 26 ቀን 2014
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ
አዲስ አበባ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.