የሃይማኖት ተቋማትን ዒላማ በማድረግ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን በተመለከተ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂዎች፣ የሰባቱ አባል የሃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የጉባኤው የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዘጋጅነት የተካሄደው ውይይት በሃይማኖት ተቋማት የእርስ በእርስ ግንኙነትና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ እየተፈጠሩ ባሉ ችግሮች በተለይም የሃይማኖት ተቋማትን ዒላማ በማድረግ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን በማስመልከት ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱ ያለመከባበር መሰረታዊ ችግሮች መንስኤያቸውን በመለየትና የጋራ የመፍትሔ ሃሳቦችን በማፍለቅ የተቋማቱን የእርስ በእርስ ግንኙነት ማጠናከርን ዓላማ ያደረገ እንደነበር ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision