Fana: At a Speed of Life!

የእስቴ ወረዳ የሚሊሻ አባላት ወደ ግንባር ዘመቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን የህወሓት ግፍ “በቃ” ያሉ የደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ የሚሊሻ አባላትና ነዋሪዎች ወደ ጦር ግንባር እየዘመቱ ነው፡፡

ዘማቾቹ ÷አሸባሪው ኃይል ሀገር ለማፍረስ የአማራን እና አፋርን ክልሎች በመውረር የግፍ ግፍ እየፈጸመ በመሆኑ፥ ግፉን ለማስቆም የደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ በሥራ ሃላፊዎች የተመራ የሚሊሻ፣ የፖሊስና ሕዝባዊ ሠራዊት አባላት ወደ ወደ ግንባር መትመም መጀመሩ ነው የተመላከተው፡፡

የአሸባሪው ኃይል ጭካኔ በእያንዳንዱ ደጅ መድረስ የለበትም በማለት ዘማቾቹ በነቂስ መነሳታቸውን የገለጸው የእስቴ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ነው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.