Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ አጎዋን በተመለከተ ያሳለፈችውን ውሳኔ መልሳ እንድታጤነው መንግስት ጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ከሜሪካ የቀረጥ ነፃ ዕድል የንግድ ስርዓት (አጎዋ) ተጠቃሚነቷ እንድትተገድ ያስተላለፈችውን ውሳኔ መልሳ እንድታጤነው መንግስት ጠየቀ።
 
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአጎዋ ዕድልን በሚመለከት የአሜሪካ መንግስት ባሳለፈው ውሳኔ ላይ መግለጫ አውጥቷል።
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፥ ውሳኔው አግባብነት የሌለው እና የአሜሪካ መንግስት አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ መሆኑን አስረድቷል።
ውሳኔው አሸባሪውን ቡድን የሚያበረታታ እና ኢትዮጵያውያን ከድህነት ለመውጣት የሚያደርጉትን ጥረትና ፍላጎት የሚጎዳ መሆኑንም አስታውቋል።
 
በኢትዮጵያ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ባለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ የአሜሪካ መንግስት ያለውን ስጋት እንደሚረዳም ሚኒስቴሩ በመግለጫው ጠቁሞ፥ይሁን እንጂ ይህ ስጋት ኢትዮጵያን ከአሜሪካ የቀረጥ ነፃ ዕድል የንግድ ስርዓት (አጎዋ) ተጠቃሚነት ለማገድ በቂ ምክንያት አለመሆኑን ነው ነው ያስረዳው ፡፡
 
እገዳው ከ200 ሺህ በላይ አነስተኛ ገቢ ያላቸው እና ከጉዳዩ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው በተለይም ሴቶችን ተጎጂ እንደሚያደርግ ተጠቅሷል፡፡
 
አሜሪካ ከግጭቱ ጋር ተያይዞ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ እንዲዳረስ መንግስት በሁሉም ዘርፍ እያደረገ ያለውን ጥረት እውቅና አለመስጠቷ እንዳሳዘነውም ሚኒስቴሩ በመግለጫው አንስቷል፡፡
 
ኢትዮጵያን ከአጎዋ ማገድም የተባለውን ችግር በየትኛውም ሁኔታ ሊፈታው እንደማይችልም ነው ሚኒስቴሩ ያብራራው፡፡
ከዚህ አንጻር የአሜሪካ መንግስት ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤነው መግለጫው አጽንኦት ሰጥቶ ጠይቋል።
 
ለአፍሪካ ዕድገት ከቀረጥ ነፃ ዕድል የንግድ ስርዓት (አጎዋ) ዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላላቸው አገሮች በአሜሪካ መንግስት የተሰጠ ዕድል መሆኑ ይታወቃል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.