Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ትህነግ የተሰነዘረብንን ጥቃት መክተን የአገራችንን አንድነት እናስጠብቃለን – የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

 

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 20፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል።

በአሸባሪው የትህነግ ኃይል የተሰነዘረብንን እኩይ ጥቃት መክተን የአገራችንን አንድነትና ሉዓላዊነት እናስጠብቃለን።

ይህ የሽብር ቡድን በአማራ እና በአፋር ህዝቦቻችን ላይ ባደረሰው ወረራ ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችንን ከመኖሪያ ቀዬአቸውና ከንብረታቸው በማፈናቀልና በመዝረፍ ፣ ሴት እህቶቻችንን በመድፈር እና የአለም አቀፍን ሕግ ጥሶ ህጻናትህ የእሳት እራት ማድረጉ ዘግናኝ ግድያዎችን ጭካኔ በተሞላበት በመፈጸም አሳይቷል፡፡

አሸባሪው የትህነግ ኃይል ከተላላኪዎች ጋር በማበር ኢትዮጵያን ለመበተን የፎከረበትን ህልሙን ለማሳካት ፣ ያለውን ኃይል ሁሉ ማሰማራት ብቻ ሳይሆን ከአገራችንን ጠላቶች ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል።

በአገር ሉዓላዊነት ላይ ፈጽሞ ከማንም ጋር የማይደራደር የኢትዮጵያ ህዝብ በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይለያይ ፣ የትህነግ የሽብር ቡድን የሰነዘረበትን እኩይ ጥቃት በአንድነት እየቀለበሱ ይገኛሉ፡፡

ጁንታው በሀገራችን ህዝብ መካከል ያለውን ወንድማማችነት ለማዳከም ያላሰራጨው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እና የጥላቻ መርዝ አልነበረም የሀገራችን ህዝብ ጸር የሆኑ ፣ የአገራችንን ሰላምና መረጋጋት ለአደጋ የሚያጋልጡ የውስጥና የውጭ ጠላቶችን ለመቀልበስ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በአንድነት ቆመው እየተፋለሙ ይገኛሉ፡፡

የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የትህነግ አሸባሪ ቡድንን ለመደምሰስ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመደገፍ ከዚህ በፊት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በተለያዩ ጊዜያት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን ከማድረጉም በተጨማሪ ክልላችን የፀጥታ አካላትን ግንባር ድረስ በመላክ ሀገር በመዳኑ ዘመቻ ላይ እየተሳተፈ ሲሆን በርካታ የክልላችን ወጣቶችም የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ ማድረግ ተችሏል ነው ያለው በመግለጫው።

በቀጣይም መላው የክልሉን ህዝብ በማስተባበር የገንዘብ ፣ የቁሳቁስና መከላከያ ሊቀላቀሉ የሚችሉ ወጣቶችን ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

የክልላችን ህዝብ እና መላው የፓርቲያችን አባላት ልክ እንደ ትናንትናው አንድነታችሁን ጠብቃችሁ ፣ የአገራችን ጸር የሆኑ ኃይሎችን በማስወገድ አገራችንን ብልጽግና እንደምታሳኩ ጥርጥር የለውም፡፡

በመጨረሻም በህዝቦች መካከል ጥርጣሬን የሚረጩና ጥላቻን የሚያሰራጩ የጥፋት ኃይሎችን በመታገል፣ ለክልላችን ልማት በመደማመጥና በአብሮነት መስራት ከየትኛውን ጊዜ በላይ አሁን አስፈላጊ ነው፡፡

በተለይም ከክልላችን የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር የአካባቢያችሁን ሰላምና መረጋጋት በንቃት እንድትጠብቁና ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እያደረጋችሁ ያላችሁትን ድጋፍ ከመቼውም ግዜ በላይ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.