የቆጋ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ተስፋ ሰጭ ነው-ዶ/ር እዮብ ተካልኝ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የቆጋ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ተስፋ ሰጭ ነው ሲሉ የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታው ዶክተር እዮብ ተካልኝ ገልጹ።
ዶክተር እዮብ ተካልኝ ይህንን የተናገሩት የፌደራልና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ በቆጋ መስኖ ፕሮጀክት የለማ የሰብልና ፍራፍሬ ልማት ጉብኝት እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ነው።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደረጃ የአማራ ክልል የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው፥ የበቆሎ ሰብል ከተሰበሰበ የስንዴ አትክልትና ፍራፍሬ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ወይዘሮ አይናለም አያይዘውም በአርሶ አደሮች የተነሱ የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ ችግሮች በቀናት ውስጥ መልስ ያገኛሉ ብለዋል።
በተጨማሪም በጉብኝት የተገኙ እንግዶች አርሶ አደሮቹ ወደ ኢንቨስተር ደረጃ እንዲሸጋገሩ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
“እየተዋጋን ! እናመርታለን ! በጦርነት ያጣነውን ምርት እናካክሳለን” በሚል መሪ ቃል በሰሜን ሜጫ ወረዳ አንጉቲ ቀበሌ የ2013/14 የምርት ዘመን የሰብል ልማት የበቆሎ ምርት ክላስተር ጉብኝት እየተካሄደ ነው።
21 ሺህ 718 ሄክታር መሬት በክላስተር የበቆሎ ምርት የተሸፈነ ሲሆን፥ 1 ነጥብ 75 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል።
በሰላም አስመላሽ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግ