ሕወሓት በፈፀመው ግፍ ማኅበራዊ ፣ ስነ-ልቦናዊና ሰብዓዊ ጉዳት ደርሷል – ዶክተር እንዳለ ኃይሌ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ሕወሓት በሰሜን ወሎና ሌሎችም አካባቢዎች በፈፀመው ግፍ በነዋሪዎች ላይ ከፍ ያለ ማኅበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ሰብዓዊ ጫና እና ጉዳት መድረሱን የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ኃይሌ ተናገሩ።
ዶክተር እንዳለ አሸባሪው ሕወሓት ተቆጣጥሯቸው በነበሩት አካባቢዎች ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፣ ከፍተኛ የሆነ የማኅበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊና የሰብዓዊ ጫና ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።
በአካባቢው ያለው ኅብረተሰብም ለጤና ችግር፣ ለረሀብና መሰል ቀውሶች ተጋልጧል ሲሉ ተናግረዋል።
አሁን ላይ ከአካባቢዎቹ ተፈናቅለው ያሉ ነዋሪዎች በራሳቸው አምርተው፣ እራሳቸውን ችለው በሞቀ ጎጆ ውስጥ የነበሩ ዜጎች አሁን ላይ ሜዳ ላይ እና በመጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉም ነው ያሉት።
አያይዘውም እየደረሰ ያለው ስነ-ልቦናዊ ጉዳት እና ጫናም ከፍ ያለ መሆኑን አስረድተዋል።
ከቤትና ንብረታቸው ተፈናቅለው፣ ለማኅበራዊ ፣ ስነ-ልቦናዊና የሰብዓዊ ጫና እና ጉዳት ተዳርገው የሚገኙ ዜጎችም እጅግ በጣም ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸው መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
ይህም እንደ አገር ጫናው በዛው ልክ ከፍ ያለ ነው ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
–
Distribution Score
Boost Post
Like
Comment
Share