በኦሮሚያ ክልል ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ይሰጣል – አቶ አወል አብዲ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የህዝብ እንግልት እና ሌብነትን በማስወገድ ጥራቱን የጠበቀ እና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ ገለጹ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ምክትል ርዕስ መስተዳድሩ፥ በሃገሪቱ ለውጥ እንዲመጣ ገፊ ከሆኑ መንስኤዎች መካከል ብልሹ አሰራር፣ ህገ ወጥ የአገልግሎት አሰጣጥ እና ስርዓት አልበኝነት ማስወገድ መሆኑን አስታውሰዋል።
በኦሮሚያ ክልልም በአዲስ ምዕራፍ ተመርጦ የተመሰረተው መንግስት የህዝብን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ ላይ ቅድሚያ ሰጥቷል ነው ያሉት።
በክልሉ የመሬት አቅርቦት፣ ኢንቨስትመንት፣ ገቢዎች፣ ንግድን ጨምሮ ሌሎች ዘርፎችም የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር እንደታየባቸው በጥናት መለየቱን ጠቁመዋል።
ይህን ለማስተካከል ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ የተፎካካሪ ፓርቲዎችን ጨምሮ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ወካይ የሆነ የአመራር ምደባ እየተጠናቀቀ መሆኑንም አስረድተዋል።
ቀልጣፋ የአገለግሎት አሰጣጥ መዘርጋት፣ ሰላም እና ፀጥታ ማስከበር እንዲሁም የግብርና ልማት ስራዎችን ማስፋፋት ደግሞ ከአዲስ ተመዳቢ አመራሮች ከሚጠበቁ ስራዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል።
በታችኛው የክልሉ መንግስት መዋቅር የተመደቡ አመራሮችም ህዝብ መስማት እና ለህዝቡ ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸውን በተግባር በየሶስት ወሩ በሚደረግ ግምገማ እርማት ይደረጋል ነው የተባለው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!