Fana: At a Speed of Life!

የቡና ፍሬ በሽታ በደቡብ ኢትዮጵያ ቡና አብቃይ ቦታዎች ተከስቷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡና ፍሬ በሽታ በደቡብ ኢትዮጵያ አንዳንድ የቡና አብቃይ ቦታዎች መከሰቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ምክክር ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ፈቶ ኢሲሞ ÷ ወቅቱን ጠብቀው ከሚከሰቱ የቡና በሽታና ተባዮች የቡናን ሰብል መከላከልና ምርትና ምርታማነቱን ማሳደግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቡና ፍሬ በሽታ ፍሬውን የሚያበሰብስ እና የሚያራግፍ ሲሆን፥ የምርምር ቡድን በማዋቀር የዳሰሳ ጥናት እየተደረገ መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል።

ከዳሰሳ ጥናቱም የቡና ፍሬ በሽታ መከሰቱ እንደታወቀ እና በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የተሻሻሉ በሽታውን የሚቋቋሙ ዝርያዎችን ያልተጠቀሙ አርሶ አደሮች ለቡና ፍሬ በሽታ እንደተጋለጡ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመላክቷል፡፡

ጥናቱ በተካሄደበት ደቡብ ክልል ጌዶ ዞን 11 ቀበሌዎች በ48 የቡና ማሳዎች ላይ በሽታው ተከስቷል፡፡

በመሆኑም ኢንስቲቲዩቱ ከዚህ በፊት ያቀረባቸውን በሽታውን የሚቋቋሙ የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን በመጠቀም በሽታውን መከላከል እንደሚቻል እና እነዚህን ዝርያዎች አርሶ አደሮች መጠቀም እንዲችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.