Fana: At a Speed of Life!

በአብዬ የሚገኘው የሰላም አስከባሪ ሠራዊት ተልዕኮውን በብቃት እየፈፀመ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአብዬ የሚገኘው የ24ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ 4ኛ ኤፒሲ ሻምበል የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በአስተማማኝ ሁኔታ እየፈፀመ እንደሚገኝ ተመላከተ።
 
የሻምበሉ ዋና አዛዥ ሻለቃ በርሄ ሀጎስ÷መነሻችንን ሀጎግ በማድረግ ሩቤክ፣አያክቶኒ፣ማዬም፣አባቶክ እና ሌሎች እስከ 50 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ቀጣናዎችን የማታ ፣ የቀንና የለሊት ቅኝት በማድረግ ቀጣናው የተረጋጋና ሰላም የሰፈነበት እንዲሆን እያደረግን እንገኛለን ብለዋል።
 
በተጨማሪም ለወታደራዊ ታዛቢዎች እና ለእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች በየጊዜው ከምናደርገው የእጀባ ስራ ባሻገር፣ በከተማዋ በሚገኘው ኤርፖርት፣ የተለያዩ እንግዶች ሲመጡ ጥበቃ በማድረግ ኃላፊነታችንን በብቃት እየተወጣን እንገኛለን ነው ያሉት።
 
የሀጎግ ከተማ ነዋሪዎችም የዕለት ተዕለት የንግድ እንቅስቃሴያቸው እንዳይስተጓጎል ከከተማው የፀጥታ አካል ጋር በመቀናጀት ሠላምን የማረጋገጥ ስራ እየሠሩ እንደሚገኝም ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.