Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ጎንደር ዞን ዘማች የሚሊሻ አባላት አሸኛኘት ተደረገላቸው

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ስር ከሚገኙ 18 ወረዳዎች የተውጣጡ የሕዝባዊ ሠራዊት አባላት ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ግንባር ለመዝመት በነፋስ መውጫ ከተማ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

የሕዝባዊ ሠራዊት አባላት ሀገር እና ሕዝብ የጣለባቸውን አደራ በጀግንነት እንዲወጡ፤ ደጀን የሆነው ሕዝብ፣ የዞን አስተዳደሩ እና በየደረጃው የሚገኝ የመንግሥት መዋቅር ደግሞ የዘማች ቤተሰቦችን በኃላፊነት እንዲንከባከብ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ የአማራ ክልል አካባቢ ጥበቃ ቢሮ ኅላፊ አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ ÷ከጉና ተራራ ግርጌ ከጋፋት ራስጌ የመነጫውን ጥንታዊ ታሪካችሁን አስጠብቃችሁ እንደምትመለሱ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይርጋ ሲሳይ ÷በዞኑ የተወሰኑ ወረዳዎች ወረራ ፈጽሞ የነበረውን ቡድን በማጽዳት በኩል እርብርብ ላደረጉ የወገን ጦር አባላት ምስጋና አቅርበው ወራሪው ኀይል ሙሉ በሙሉ እስኪ ደመሰስ ድረስ ዘመቻው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ዘማች የሚሊሻ አባላቱ በዘመቻው የወገን ጦር የሰጣቸውን ግዳጅ እና ኅላፊነት በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.