Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን በሁለት ህፃናት ላይ የፖሊዮ ቫይረስ ታየ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በጅማ ዞን በሁለት ህፃናት ላይ የፖሊዮ ቫይረስ መታየቱን የዞኑ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በጽህፈት ቤቱ የቤተሰብ ጤና አስተባባሪ አቶ ጣሰው ብርሃኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ቫይረሱ በዞኑ ዴዶ እና ጉማይ ወረዳዎች ከአምስት ዓመት በታች ባሉ ሁለት ህፃናት ላይ ነው የታየው።

ህፃናቱ ላይ የልምሻ ምልክት መታየቱንና ተከትሎ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው አስተባባሪው ተናግረዋል።

በዞኑ የፖሊዮን በሽታ ለመከላከል በየዓመቱ ክትባት ሲሰጥ እንደነበር የጠቆሙት አስተባባሪው÷ በርካታ ህፃናትን መታደግ መቻሉን ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ አሁን ላይ ቫይረሱ በዞኑ መታየት ጀምሯል ነው ያሉት።

በመሆኑም የፖሊዮ በሽታን ለመከላከል ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት፥ ከአምስት አመት በታች ላሉ 700 ሺህ ህፃናት ክትባቱ እንደሚሰጥ ከዞኑ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በሙክታር ጠሀ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.