አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቻይንኛን ቋንቋ በሁለተኛ ዲግሪ ሊሰጥ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የቻይንኛ ቋንቋን በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
ቻይንኛ በሁለተኛ ዲግሪ ሲሰጥ÷ በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት እመቤት ሙሉጌታ እንዳሉት÷ የመርሃ ግሩ መከፈት የሁለቱን ሀሃገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ያጠናክራል፡፡
ለመርሃግብሩ አድናቆትና ድጋፍ አለን ያሉት ምክትል ፕሬዚደንቷ÷ ፕሮግራሙ ተገምግሞ በሴኔት መጽደቁን ተናግረዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የቻይንኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ዲግሪ እንደሚሰጥ አስታውሰው÷ የአሁኑ መርሃ ግብር በዚሁ ዘርፍ የሰለጠኑ ተማሪዎችን በቋንቋው ክህሎት ይበልጥ አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ ያስችላል ብለዋል ሲል ሽንዋ ዘግቧል፡፡
በሻምበል ምህረት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!