Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ መመሪያ አዘጋጀች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የሀገሯን የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ግቦች በዝርዝር ያመላከተ መመሪያ አወጣች፡፡

በግቦቹ መሠረት እስከ ፈረንጆቹ 2025 ድረስ ÷ የቻይና ጥብቅ ተፈጥሯዊ አካባቢዎች፣ በዋናነት ብሔራዊ ፓርኮች የሀገሪቷን 18 በመቶ ያህል መሬት መሸፈን አለባቸው ተብሏል፤ የሀገሪቷ የደን ሽፋን መጠን ደግሞ 24.1 በመቶውን እንደሚሸፍን በዝርዝር መመሪያው ተመላክቷል፤ በሳር የሚሸፈነው መሬት ደግሞ 57 በመቶ እንደሚሆን ነው የተገለጸው፡፡

የቻይና መንግስት ÷ የሀገሪቷን 55 በመቶ ለሚሸፍነው እርጥብ መሬት ፣ 35 በመቶ ያህሉን ለሚሸፍኑት ተፈጥሯዊ የባሕር ጠረፎች እንዲሁም 77 በመቶ ለሚሆኑት የሀገሪቷ የዱር አራዊት ዝርያዎች ጥብቅ ጥበቃ እንደሚያደርግላቸው ሲጂቲ ኤን አመላክቷል።

በግምት 92 በመቶ ያህሉ የሀገሪቷ ሥነ-ምህዳር ጥበቃ ይደረግለታልም ተብሏል፡፡

በዓለማየሁ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.