የነብዩ መሃመድ የልደት በዓል በአንዋር መስጂድ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) 1ሺህ 496ኛዉ የነብዩ መሃመድ የልደት በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡
በበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የአንዋር መስጂድ ኢማም ሃጅ ጣሃ ሃሩን÷ በዓሉን ስናከብር የነብዩ መሃመድን አስተምህሮ በመከተል ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
አክለዉም በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ ያለዉ ለሌለዉ በማካፈል፣ አንድነታችንን በማጠናከርና የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍ መሆን አለበት ብለዋል፡፡
በበዓሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እድሪስን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!