Fana: At a Speed of Life!

የቦለቄ ምርትን በማሳደግ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ማሳካትና ወደ ውጭ መላክ ይገባል – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተመራው ልዑክ በምእራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ወረዳ የቦለቄ ኩታገጠም ማሳን እና በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ቡልቡላ በኩታገጠም የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኘ፡፡

በጉብኝቱ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች እና የሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች ተገኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምእራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ወረዳ ባደረጉት ጉብኝት እንደገለጹት÷ የቦለቄ ምርትን በማሳደግ የሀገር ውስጥ የምግብ ፍላጎትን በማሳካት ለኤክስፖርትም መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በስፍራው የተገኙ አርሶ አደሮችም÷ በሄክታር ከ30 እስከ 40 ኩንታል እንደሚያኙ ገልጸዋል፡፡

ምእራብ አርሲ በቦለቄ ምርት ሰፊ አቅም ያለው መሆኑ በጉብኝቱ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ቡልቡላ በክላስተር የለማ የስንዴ ማሳን ጎብኝተዋል።

በስፍራው 650 ሄክታር መሬት በምርጥ ዘር ምርት ተሸፍኗል። ይህ ቦታ ከዚህ በፊት ምርት የማይመረትበት እና የታጠረ እንደነበረ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካናቸው በዚያው በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚቱሉ ጂዶ ኮምቦለቻ ወረዳ ቡልቡላ በክላስተር የለማ የቦቆሎ ማሳን ጎብኝተዋል።

በለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.