አሸባሪው ሸኔ በፈጸመው ጥቃት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) -በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ከተማ ፅንፈኛው የአሸባሪ ቡድን ሸኔ ጥቅምት 1 እና 2 በንፁሃን ላይ በከፈተው ጥቃት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል ።
ቡድኑ ከህውሃት የሽብረ ቡድን ጋር ህብረቱን ካረጋገጠ በኋላ በብሄር ብሄረሰቦች ላይ ትንኮሳ በማድረግ ግጭቶችም የብሄር መልክ እንዲይዙ እየሰራ ይገኛል ብለዋል የቢሮው ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ ።
ኃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ሸኔ በአካባቢው ከሚንቀሳቀስ ሌላ የሽፍታ ቡድን ጋር በመተባበር በሀሮ ከተማ በከፈተው ጥቃት የ15 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የንብረት ውድመት እንዳደረሰ እንዲሁም 967 አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ተናግረዋል፡፡
የክልሉ መንግስት ተጨማሪ የፀጥታ ሀይል ወደ ስፍራው በማሰማራት ወረዳውን እና ከተማውን የማረጋጋት ስራ እየሰራ ሁኔታውን የተቆጣጠረ ሲሆን ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል ።
በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ እነዚህ ቡድኖች የብሄርን ሳይሆን የሶስተኛ ወገን ዓላማ እያስፈፀሙ በመሆኑ ህብረተሰቡ እኩይ ተግባራቸውን ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የመታገል እና ፀጥታውን የማስጠበቅ ስራውን እንዲያግዝ የቢሮ ኃላፊው ጠይቀዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!