Fana: At a Speed of Life!

ያለ አሽከርካሪ የሚሰራ የእቃ ማመላለሸ ተሽከርካሪ ሙከራውን ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው ያለ አሽከርካሪ የሚሰራ የእቃ ማመላለሽ ተሽከርካሪ በአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ ሙከራ እንዲያደርግ ፈቃድ አገኘ።

ተሽከርካሪው የአሽከርካሪ ወይም የሰው እገዛ ሳያስፈልገው አገልግሎት ይሰጣል ነው የተባለው።

ኑሮ በተባለው ኩባንያ የተሰራው ተሽከርካሪ መሪን ጨምሮ ለመሽከርከር የሚያገለግሉት የነዳጅ መስጫና ፍሬን እንዲሁም የእይታ መስታወትን (ስፖኬ) ያለ አሽከርካሪ በራሱ ይጠቀማል።

የአሜሪካ የትራንስፖርት ሚኒስቴርም ተሽከርካሪው በቴክሳስ ሙከራውን እንዲያደርግ ፈቃድ ሰጥቶታል።

አር 2 የሚል ስያሜን ያገኘው ይህ የእቃ ማመላለሻ፥ የኩባንያው ሁለተኛው ትውልድ ተሽከርካሪ ሲሆን በሆስተን ቴክሳስ ሙከራ እንደሚያደርግ ነው የተነገረው።

የእቃ ማመላለሻውን ለመሞከር ተሽከርካሪውን መቆጣጠር የሚያስችሉ ክፍሎችን ማሟላት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

ሆኖም የእቃ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ፍጥነት በሰዓት ከ25 ኪሎ ሜትር እንዳይበልጥ የአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስቴር አስጠንቅቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.