በአየር ኃይል ምስራቅ አየር ምድብ በስራ አፈፃፀማቸው ምስጉን ለሆኑ የምድቡ ሰራዊት አባላት ማዕረግ ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፥ 2014 ዓ.ም( ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ አየር ኃይል ምስራቅ አየር ምድብ በስራ አፈፃፀማቸው ምስጉን ለሆኑና የመቆያ ጊዜያቸውን በጥሩ ወታደራዊ ዲሲፒሊን ለሸፈኑ የምድቡ ሰራዊት አባላት ማዕረግ ሰጠ።
ለተሿሚዎቹ ማዕረግ በማልበስ የስራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት የምስራቅ አየር ምድብ አዛዥ ኮ/ል አበበ ለገሰ ፣ አየር ምድቡ ህግን በማስከበር ዘመቻ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በግንባር ቀደምትነት በመሳተፍና የህወሃት አሸባሪ ቡድንን በመደምሰስ አኩሪ ጀብድ ፈፅሟል ብለዋል።
የእለቱ ተሿሚዎች በተሰጣችሁ የማዕረግ ሹመት በመበረታታት አሸባሪ ቡድኑን ለማጥፋት በሚደረገው ቀጣይ የህልውና ዘመቻ ትልቅ ግዳጅ ይጠብቃችኋል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገፅ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!