Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ በክልልነት መዋቀር እንፈልጋለን የሚለው በአብላጫ ድምፅ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ውስጥ የነበሩ አምስት ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ህዝበ ውሳኔ መስከረም 20/2014ዓ.ም ተካሂዶ በክልልነት መዋቀር እንፈልጋለን የሚለው በአብላጫ ድምፅ ድጋፍ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
በኮንታ ልዩ ወረዳ፣ የምዕራብ ኦሞ ዞን፣ የቤንች ሸኮ ዞን፣ የዳውሮ ዞን፣ የከፋ ዞን እና የሸካ ዞን ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ወጥተው የጋራ አንድ ክልል መመስረታቸው በህዝበ ውሳኔ መደገፋቸውን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ በመግለጫው ተናግረዋል።
ለህዝበ ውሳኔ ድምፅ ለመስጠት 1 ሚሊየን 344 ሺህ 622 ዜጎች ተመዝግበው 1ሚሊየን 262ሺህ 679 ዜጎች ወይም ከተመዘገቡት 93 ነጥብ 9 በመቶ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፡፡
በዚህ መሰረት ከቀረቡት ሁለት አማራጮች 1ሚሊየን 221 ሺህ 92 ዜጎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች በሚል የጋራ አንድ ክልል ለመመስረት እደግፋለሁ በማለት ወስነዋል።
በዚህ መሰረት ምርጫ ቦርድ ውጤቱን ለፌደሬሽን ምክር ቤት የሚያቀርብ መሆኑን በመግለጫው ተነስቷል።
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.