Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ቀና ብላ እንድትሔድ የሚያደርጋት ታሪክ እየተደገመ ነው -የታሪክ ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በአለም አደባባይ ቀና ብላ እንድትሔድ የሚያደርጋት የነጻነት ታሪክ በአሁኑ ትውልድ እየተደገመ ነው ሲሉ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁራን ገለጹ፡፡
የምዕራባዊያን ኢትዮጵያን የማንበርከክ ሴራ ዛሬ የጀመረ ሳይሆን ከጥንት ጀምሮ የነበረ ታሪክ መሆኑን የገለጹት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪው ዶክተር ጸሀይ ምክሬ፥ ኢትዮጵያዊያን የሃገራቸውን ልዑአላዊነት ላለማስደፈር ባደረጉት ተጋድሎ ነጻና ክብሯን የጠበቀች ሃገር ማስረከብ ችለዋል ብለዋል፡፡
የውጭ ሃይሎችን ጫና ተቋቁማ ልዑአላዊነቷን የጠበቀችና የድፍን ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ምሳሌ መሆን የቻለች ኢትዮጵያ ትፈጠር ዘንድ ኢትዮጵያዊያን በሀገር ጉዳይ በምንም ሁኔታ ብርቱ አንድነት ያላቸው ህዝቦች መሆናቸው ትልቅ ዋጋ ነበረው ሲሉ ዶ/ር ጸሀይ ምክሬ ገልጸዋል፡፡
ይህም በአድዋ በማይጨው ና በካራማራ ጦርነቶች የታዬ ደማቅ ታሪክ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዛሬም ይህ የኢትዮጵያዊያን ልዑአላዊነትን ያለማስደፈር ታሪክ እየተደገመ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ጸሀይ ምክሬ፥ አሁን በውጭ ሃይሎች የውክልና ጦርነት የከፈተውን አሸባሪውን ሕወሓትን ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ ለማምከን ኢትዮጵዊያን እያሳዩት ያለው አንድነት ለዚህ ሁነኛው ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ከኢትዮ ሶማሊያ ጦርነት ጋር የሚመሳሰል ነው ያሉት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር የሆኑት አለማየሁ አብረሃም በበኩላቸው ፥በወቅቱ የዚያድ ባሬ መንግስት ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ መሆኗን እንደአጋጣሚ ተጠቅሞ ወረራ ቢፈጽምም ኢትዮጵያዊያን ያለባቸውን ችግር ወደጎን ትተው በአንድ ጥሪ አንድ ሆነው ሃገራቸውን መታደግ ችለዋል ብለዋል፡፡
ዛሬም በኢትዮጵያ የውጭ ሃይሎች አሸባሪውን ቡድን እየጋለቡ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ ቢሞክሩም ኢትዮጵያዊያን በሃገር ልዑኣላዊነት ጉዳይ በምንም ሁኔታ አንድ መሆናቸውን ያሳዩበትን ታሪክ እየደገሙት ነው ሲሉ መምህር አለማየሁ አብረሃም ገልጸዋል፡፡
የሀገር ህልውናን ለማስጠበቅ ኢትዮጵያዊያን እያሳዩት ያለው አንድነት የአባቶችን ታሪክ የደገመ ከመሆኑም በላይ ሕወሃት ሊያጠፋው የሰራበት የሃገር ፍቅር ዛሬም ህያው መሆኑን ያስመሰከረ እውነት መሆኑን የታሪክ ምሁራኑ ተናግረዋል፡፡
በተስፋየ ምሬሳ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
902
People Reached
168
Engagements
Boost Post
149
4 Comments
8 Shares
Like

Comment
Share
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.