ከብልጽግና ፓርቲ ውጪ ሶስት እጩዎች በሚኒስትር ደረጃ ሹመታቸው ጸደቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያቀረቧቸው ከብልጽግና ፓርቲ ውጪ የሆኑ ሶስት የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችን በሚኒስትር ደረጃ ሹመታቸው ጸድቋል፡፡
በዚህም መሰረት የኢዜማ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡
በተመሳሳይ የአብን ሊቀመንበር የሆኑትን ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ሲሾሙ ÷ የኦሮሚያ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ቀጀላ መርዳሳ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!