አዲሱ መንግስት የሀገር ህልውናን ለማስጠበቅ እና ሰላም ለማስፈን ቅድሚያ ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል-የባህር ዳር ነዋሪዎች
አዲስ አበባ መስከረም 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የተሚመሰረተው መንግስት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ እና ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ላይ ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች አሳሰቡ።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች፥ኢትዮጵያ የተጋረጡባትን የውስጥ እና የውጭ ጫናዎች በመቋቋም የህዝብ ይሁንታና አመኔታን ያገኘ አዲስ መንግስት በሰላም በመመስረቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
አዲስ የተመሰረተው መንግስትም አሁን ላይ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚስተዋለውን የሰላምና የጸጥታ ችግር መፍታት ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ነው ያሉት።
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን ያነሱት ነዋሪዎቹ፥አዲሱ መንግስት ለዚህ ችግር አስቸኳይ መፍትሄ ለመስጠት በትኩረት መስራት እንዳለበት ጠይቀዋል።
ለዚህም ወራሪው የትህነግ ቡድን ለኢትዮጵያ ስጋት በማይሆንበት ደረጃ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መደምሰሱ ለነገ የማይባል ጉዳይ እንደሆነ ነው የገለጹት።
በተመሳሳይ የህወሓት ተላላኪ በሆኑት ኦነግ ሸኔ ፥ ጽንፈኛ የቅማንት ታጣቂዎች እና በቤኒሻንጉል ጉምዝ በሚንቀሳቀሱ ሽፍታዎች ላይ መንግስት የማያዳግም እርምጃ መውሰድ አለበት ነው ያሉት።
በወራሪው የትህነግ ቡድን እና ሸኔ አረመኔያዊ ድርጊት ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ያሉት ነዋሪዎቹ፥ አዲሱ መንግሥት እነዚህን ዜጎች ወደ ቀደመ ህይወታቸው በዘላቂነት መመለስ እና የወደሙ የህዝብ መገልገያ ተቋማትን መልሶ መገንባት ይጠበቅበታል ብለዋል።
አዲስ የተዋቀረው መንግስት በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የልዩነት አስተሳሰብ እና ጽንፈኝነት በማስወገድ አንድነትን ማጠንከር ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበትም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ አድነት በዘላቂነት በማጠናከር እና የግዛት አንድነቷን በማስጠበቅ በሀገር ውስጥና በውጭ ጠላቶች ታፍራ እና ተከብራ እንድትኖር ማስቻል ይገባል ነው ያሉት።
የህግ የበላይነትን ማስከበር እና ሁሉም ዜጋ በየትኛውም የሀገሪቱ ከፍል በነጻነት ተንቀሳቅሶ መስራት እና ህይወቱን መምራት የሚችልበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠርም ከአዲሱ መንግስት እንደሚጠበቅ ነዋሪዎቹ አንስተዋል።
አሁን ላይ የኑሮ ውድነት የመላ ኢትዮጵያውያንን ቤት ያንኳኳ መሆኑን የገለጹት ነዋሪዎቹ ፥ በቀጣይ የኢኮኖሚ አሻጥሮች በመበጣጠስ የተፈጠረውን አላስፈላጊ የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ማረጋጋትም የአዲሱ መንግስት የቤት ስራ ነው ብለዋል።
የሀገር ውስጥና ውጭ ባንዳዎችን በተቀናጀ መልኩ በመመከት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ላይ መስራት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
በተለይም የውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ እየፈጠሩት ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጫና ለመቋቋም አዳዲስ ፖሊሲ እና ስትራቴጂዎችን መተግበር እንደሚገባ ነው የተናገሩት።
በህዝብ ዘንድ ለሚነሱ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ እና መፍትሄ መሥጠት ያስፈልጋል ያሉት ነዋሪዎቹ ፥ ለዚህም በየደረጃው የሚመደቡ ሥራ ሃላፊዎችን እውቀትን እና ክህሎትን መሠረት አድርጎ መመደብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመላኩ ገድፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share