ከተሳሳተ የአወቃቀር ለዉጥ ጋር ተያይዞ ተቋርጦ የነበረዉ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ተመልሷል-የፌስቡክ ካምፓኒ
አዲስ አበባ፣መስከረም 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌስቡክ ፣ ዋትሳፕ እና ኢንስታግራም ትናንት ለስድስት ሰዓታት ያህል ከተቋረጡ በኋላ ተመልሰዋል ሲል የፌስቡክ ካምፓኒ አስታወቀ፡፡
ተቋርጦ የነበረዉ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ከተሳሳተ የአወቃቀር ለዉጥ ጋር ተያይዞ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የፌስቡክ ካምፓኒዉ በመግለጫዉ÷ የማህበራዊ ሚዲያው ተቋርጦ በነበረበት ወቅት የተጠቃሚ ግላዊ መረጃ ተጥሷል የሚል ማስረጃ የለም ብሏል፡፡
የአገልግሎት መቋረጥን የሚከታተለው ዳውደክተር÷እስካሁን በዓለም ዙሪያ 10 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚሆኑ የችግር ሪፖርቶች እንዳሉ ተናግረዋል።
የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ በመቋረጡ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ይቅርታ ጠይቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!