Fana: At a Speed of Life!

የናይጄሪያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የናይጄሪያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፍሬይ ኦኒዬማ በአዲሱ መንግስት ምስረታ ሥነ-ስርዓት ላይ ለመታደም ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ አክሊሉ ከበደና ሌሎች የሚኒስቴሩ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የ65 ዓመቱ ጄፍሬይ ኦንዬማ ከእ.አ.አ 2015 ጀምሮ የናይጄሪያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው እያገለገሉ ይገኛል።
ኦኒዬማ ከእ.አ.አ 2009 እስከ 2015 መቀመጫውን ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ባደረገው የዓለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ተቋም ምክትል ዋና ዳይሬክተር በመሆን ሰርተዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተር ከመሆናቸው በፊት ከእ.አ.አ 1985 ጀምሮ በተቋሙ በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች አገልግለዋል።
ጄፍሬይ ኦንዬማ በናይጄሪያ ታሪክ 28ኛው የአገሪቷ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሆኑ፤ ከፖለቲከኛነታቸው በተጨማሪ የሕግ ባለሙያም ናቸው።
ኢትዮጵያና ናይጄሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ በ1964 ነው።
የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪ እ.አ.አ የካቲት 2020 በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።
በህዝብ የተመረጠው ፓርቲ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ መንግስት ይመሰርታል።
ምንጭ:- ኢዜአ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.