Fana: At a Speed of Life!

የሰላም መልዕክተኞች የምርቃት ስነስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዩኒቨርስቲ የሰላም መልዕክተኞች የምርቃት ስነስርዓት ተካሂዷል።
ከተለያዩ አካባቢ የተውጣጡ ወጣቶች በላም፣ በሃገር ፍቅር እሰሴትና በጎ ፍቃደኝነት ተግባር ላይ ለ 45 ቀናት ስልጠና ሲወስዱ ቆይተው ነው ዛሬ የተመረቁት።
በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዲኤታ አለም ፀሃይ ጳውሎስ፣ የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀማል አባ ፊጣ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ፥ስልጠናው ባለፉት አመታት በተለያዩ ምክንያቶች የተጎዱ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን መልሶ ለመጠገን ታቅዶ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።
ተመራቂ ወጣቶችም የአብሮነትና የመተሳሰብ ድልድይ ሆነው ኢትዮጵያን መልሰው ለመንገባት በመታጨታቸው እድለኞች መሆናቸውን ገልፀው የተጣለባቸውን ሃላፊነት በትጋት እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባ ፊጣ በበኩላቸው፥ ሰልጣኞች ለ 45 ቀናት በዩኒቨርስቲው በነበራቸው ቆይታ የፈፀሟቸው በጎ ተግባራት ኢትዮጵያ ለወደፊት ተስፋ ሰጭ ወጣቶች እንዳሉዋት አመላካች መሆኑን ተናግረዋል።
በጅማ ዩኒቨርስቲ 5 ሺህ 605 ወጣቶች የበጎነት ለአብሮነት ስልጠና ሲከታተሉ ቆይተው ነው ዛሬ የተመረቁት።
በሙክታር ጠሃ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.