Fana: At a Speed of Life!

የበዓላት በሰላም መከበር ምስጢር የሕዝቡን ሠላም ወዳድነት ማሳያ ነው- የኢሬቻ ተሳታፊዎች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የአደባባይ በዓላት በሠላም መከበራቸው ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ለሚፈልጉ ሃይሎች ትልቅ መልዕክት እንዳለው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ታዳሚዎች ገለጹ።
ታዳሚዎቹ ኢትዮጵያን ለመበታተን ከውስጥና ከውጭ የሚደረጉ ጫናዎች በሕዝቦቿ የተባበረ ክንድ እንደሚከሽፉም ነው የተናገሩት።
የሆራ ፊንፊኔን በዓል ከኦሮሞ ባሻገር የተለያዩ ብሄርና ብሄረሰቦችም በአንድነት አክብረውታል።
በተለይ ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ወቅታዊ ችግር ተጠቅመው የራሳቸውን የፖለቲካ ፍላጎት ለማሳካት የሚፍጨረጨሩ ሃይሎች የኢትዮጵያዊያንን የአንድነት ስነ ልቦና ያልተረዱ ናቸው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ሃይማኖታዊና ሕዝባዊ በዓላት በሠላማዊ መንገድ የመከበራቸው ምስጢርም የሕዝቡን ሠላም ወዳድነትና መቻቻል ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ ላይ እየተደረጉ ያሉ የውስጥና የውጭ ጫናዎችን ለመመከት ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።
አዲስ የሚመሰረተው መንግስትም ሠላምና መረጋጋት ማስፈን ቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን እንደሚገባ ጠቅሰው ነገር ግን ሠላምን ከመንግስት ብቻ መጠበቅ ተገቢ አለመሆኑንም አንስተዋል።
በአገር ሉዓላዊነት ላይ የተጋረጠውን አደጋ መመከት ለነገ የማይባል ተግባር መሆኑንም አስተያየት ሰጪዎቹ አመለክተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.