Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሙስሊሙ ማሕበረሰብ አባላት ለተፈናቃዮች ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣መስከረም፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የሙስሊሙ ማሕበረሰብ አባላት በደሴ ለሚገኙ ተፈናቃይ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።
መሕበረሰቡን በማስተባበር ድጋፍንደሴ ከተማ ይዘው የተገኙት ባዩሽ መስጊድ ፣ነጃሽ መሰጊድ እና በመሀል ሀገር የሚኖሩ የሰሜን ወሎ አካባቢ ተወላጆች ኮሚቴዎች ናቸው።
ድጋፍን ያደረጉት ተወካዮች ባስተላለፍት መልእክት፥ ከዚህ በኋላም ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው እስከሚመለሱ የሚያደርጉትን እገዛ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
አቶ ሰይድ የሡፍ የደሴ ከተማ ከንቲባ በድጋፍ አሰጣጡ ሥነሥርዓት ላይተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ፥የተደረገው የምግብ እና ምግብ ነክ የቁሳቁስ የአልባሳት ድገፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች ብዙ ነገር ነው ብለዋል።
አቶ ሰይድ ሰለተደረገው የተቀናጀ ድጋፍና ለአስተባባሪዎች ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በእሸቱ ወ/ሚካኤል
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.