Fana: At a Speed of Life!

ኢሬቻ የተስፋና የመፃኢ እድል ብስራት ተደርጎ ይከበራል-አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ኢሬቻ የተስፋና የመፃኢ እድል ብስራት ተደርጎ ይከበራል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ ፡፡
የኢሬቻ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በበዓሉ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ÷ ኢሬቻ የተስፋና የመፃኢ እድል ብስራት ተደርጎ ይከበራል ነው ያሉት።
የኦሮሞ ህዝብ ሞጋሳና ጉዲፈቻን የመሰሉ ውብ ባህሎች ከጥንት እስከዛሬ ይዞ መቆየቱን ያነሱት ርዕሰመስተዳድሩ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን ሀገር ሰርቷል ነው ያሉት።
የገዳ ስርዓትን የመሰሉ በሀገር ግንባታ ስርአቱ ላይ ሚና የነበራቸውን እሴቶችንም ለአዲሱ ትውልድ ማሳወቅ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።
ኦሮሚያን ማልማት ኢትዮጵያን ማልማት ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ በዚህም ሁሉን አቀፍ ተግባራትን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
እንዲሁም የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መነካት የኦሮሞ ህዝብ መነካት ነው ያሉ ሲሆን ÷ የገጠሙ ፈተናዎችን ለመሻገር እንደሚሰራ ገልፀዋል።
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.