Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ከአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ስርጭትና አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሰብዓዊ እርዳታ ስርጭት ሂደት ላይ ከአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ስርጭትና አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ተወያይተዋል።
በአማራ እና አፋር ክልል ላይ እየተካሄደ ባለው የእርዳታ ስርጭት ላይ የታዩ ክፍተቶችን እና ሊወሰዱ የሚገቡ አፋጣኝ የመፍትሄ እርምጃዎች ላይ መክረዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ ለማድረስ የየዕለት ግብ የተያዘ ቢሆንም÷ ወደ ክልሉ ገብተው ባልተመለሱ የጭነት ተሽከርካሪዎች ምክንያት ሂደቱ በመስተጓጎሉ ተገልጿል፡፡
ስለሆነም ተሽከርካሪዎቹን በማስመለስ ረገድ የሰብዓዊ እርዳታ ሰጭና አቅራቢ ድርጅቶቹ ሃላፊነት ወስደው ተገቢውን አመራር በመስጠት መመለሳቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው መግባባት ላይ መደረሱን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.