አህመድ ሁሴን 1 ሚሊየን ብር የሚያስገኘውን የፋና ላምሮት የድምፃውያን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ቴሌቪዥን በፋና ላምሮት ፕሮግራም በሚያካሂደው የድምፃውያን ውድድር 1 ሚሊየን ብርና የክብር ዋንጫ የሚያስገኘውን የ8ኛው ምዕራፍ የአሸናፊዎች አሸናፊ የማጠቃለያ ውድድር አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) አሸናፊ ሆኗል፡፡
ዛሬ በተካሄደው የፍጻሜ ወድድር ዮናታን ዳመነ ሁለተኛ፣ ጌታቸው መስፍን ሦስተኛ እና ሰላማዊት ቦጋለ አራተኛ በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡
አንደኛ የወጣው የ1 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሲሆን÷ ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ለወጡት ደግሞ እያንዳንዳቸው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የ2 መቶ ሺህ ብር ልዩ ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!